Tinkish Development and Civil Society Organization
Home
About
Programs
Projects
Donors
Impact
Registry
News
Donate
Contact
Home
Blog
Article
01 September 2026
የባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫና ውይይት መድረክ ማጠቃለያ ሪፖርት
የባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫና ውይይት መድረክ ማጠቃለያ ሪፖርት
=====================================================
ድርጅታችን ጥንቅሽ ደቨሎፕመንት ኤንድ ሲቪል ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን ከዚህ ቀደም ባቀደው መርሃ ግብር መሠረት፣ እሁድ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኝ አዳራሽ ይፋዊ የድርጅቱ የትዉዉቅ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫና የባለድርሻ አካላት ውይይት መድረክን በስኬታማነት አካሂዷል። በመድረኩ ላይ ከመንግስት አካላት፣ ከባለሀብቶች፣ ከማህበረሰብ አንቂዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ተሳታፎች ተገኝተው ስለ ድርጅቱ ማንነት፣ ራዕይ፣ ተልዕኮ እንዲሁም እስካሁን ስለተከናወኑ ተግባራት ሰፊ ግንዛቤ አግኝተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት ተሳታፎቹ፣ ድርጅቱ ከ2026 እስከ 2031 ላለው ጊዜ ባዘጋጀው አምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ተመስርተው በትግራይ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች በሚዋሰኑ አካባቢዎች በጦርነት ምክንያት የተጎዱ ማህበረሰቦችን መልሶ ማቋቋም፣ የትምህርት ጥራት ማሻሻል፣ የጤናና የስነ-ተዋልዶ አገልግሎት ተደራሽነት ማሳደግ እንዲሁም ወጣቶችንና ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት ላይ ትኩረት ባደረጉ ተግባራት ላይ ገንቢ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡ መድረኩ ለወደፊት ትብብርና ለጋራ ስራዎች መሠረት የጣለ ሲሆን፣ ተሳታፎቹም ለድርጅቱ ተግባራት ያላቸውን ድጋፍ በተደጋጋሚ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም ድርጅታችን ለክፍለ ከተማው አስተዳደር ላደረገው ትብብርና ላበረከተው ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
ከሰላምታ ጋር፣
ጥንቅሽ ደቨሎፕመንት ኤንድ ሲቪል ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን
Back to News