ጥንቅሽ ደቨሎፕሜንት ኤንድ ሲቪል ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን (Tinkish Development and Civil Society Organization) በሀገራችን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሠረት (በምዝገባ ቁጥር 7825) በይፋ የተመዘገበ ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ በዋናነት በራያ አላማጣ እና በአዋሳኝ የትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች ላይ ትኩረት በማድረግ፣ በጦርነትና በተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ስትራቴጂካዊ ግቦችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ተቋማዊ ዓላማዎቻችን (Core Objectives)፦

✅ መልሶ ማቋቋም እና መሰረተ ልማት፦ በግጭት ሳቢያ የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ማቋቋም እና የወደሙ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ማደስ።
✅ ሰላም ግንባታና ውይይት፦ በአዋሳኝ አካባቢዎች በሚኖሩ ማህበረሰቦች መካከል ህዝባዊ ውይይቶችን በማመቻቸት አብሮነትን እና ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ።
✅ የትምህርት ጥራትና አቅም ግንባታ፦ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሳለጥ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ እና ለተማሪዎችና መምህራን ተግባራዊ ስልጠናዎችን መስጠት።
✅ ሁለንተናዊ የጤና ድጋፍ፦ የስነ-ተዋልዶ ጤና፣ የስነ-ልቦና ድጋፍ እና በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የመከላከል ስራዎች።
✅ የወጣቶች አቅም ግንባታ፦ ወጣቶች ከአስፈላጊ ያልሆኑ ሱሶች ተላቀው የአካባቢያቸውን የተፈጥሮ ሃብት እንዲያለሙና የስራ እድል እንዲፈጥሩ ማስቻል።
✅ ስደትን መከላከል፦ ህገወጥ ስደትን በጋራ ጥረት ለማስቀረት ከባለድርሻ አካላት ጋር በተቀናጀ መልኩ መስራት።

የአብሮነት ጥሪ!

"ጥንቅሽ" በአሁኑ ወቅት በአካባቢያችን የተደቀኑ ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ከማንኛውም በጎ አድራጊ ግለሰብ፣ ተቋም እና አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር ለመስራት በሩ ክፍት ነው። የአካባቢያችንን ልማት ለማፋጠን እና ሰላምን ለማስፈን በምናደርገው ጉዞ የእርስዎ ድጋፍ ትልቅ አሻራ ያሳርፋል።

ተቋማዊ የባንክ አካውንቶቻችን፦
🔹 Commercial Bank of Ethiopia፦ 1000749775355
🔹 Dashen Bank፦ 5090966227011
🔹 Siinqee Bank:- 1110220681213

ለበለጠ መረጃ እና ግንኙነት፦
📞 ስልክ፦ +251999248232/+25199238032
📧 Email: info@tinkishdevelopmentcso.org

ጥንቅሽ ደቨሎፕሜንት ኤንድ ሲቪል ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን
አብረን አካባቢያችንን እናልማ! ሰላምን እናስፍን!

#TinkishCSO #Development #PeaceBuilding #Ethiopia #HumanitarianAid #CivilSociety@tinkish_dcso

Back to News